Hawassa University


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


One of the top ranking first generation Universities in Ethiopia.

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በአጋርነት ተቀራርቦ መስራት ዋነኛው መሆኑን ተናግረዋል::

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ኢ/ር ፋስካ ቤተ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ኢንዱስትሪዎች በአካባቢያቸው ከሚገኙ የከ/ት/ተቋማት ጋር በትብብር እንዲሠሩ በመንግስት ህግ ከወጣ 35 ዓመታት ቢቆጠሩም ግልጽ የሆነ የሕግ ማዕቀፍና የአፈጻጸም መመሪያ ባለመኖሩ ምክንያት በጋራ ጥቅሞች ላይ ያለመተማመን ተፈጥሮ መቆየቱን አስረድተው ይሄንን የሚቀርፍ አዋጅ ቁጥር 1298/2015 ከወጣ ወዲህ ግን በአከባቢው የሚገኙ የልማት ድርጅቶች በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እያሳዩ መሆናቸውን ገልፀዋል። ዶ/ር ፋሲካ የዕለቱን መርሃግብር አስመልክቶም ይሄ መነሻ እንጂ የመጨረሻው ባለመሆኑ በቀጣይ እጅግ ተቀራርበን የምንሰራው በጣም ብዙ ሥራ አለ ብለዋል::

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ባዩ ቡንኩራ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ለዘላቂ ልማትና ሀገራዊ ዕድገት ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ እንደሀገር የተቀመጠውን የህግ ማዕቀፍ ይዘት ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአካዳሚክ ም/ዳይሬክተር ዶ/ር ደሳለኝ ግርማ ኢንስቲትዩቱ ከአጋር ኢንዱስትሪዎች ጋር በትብብር ሊሰራባቸው የሚችልባቸውን ዘርፎችና ያለውን እምቅ አቅም ለተሳታፊዎች አብራርተዋል::

በዚህ አውደ ርዕይ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲና ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተጋበዙ የጨርቃ ጨርቅ ዲዛይንና ስፌት ተማሪዎች የፋሽን ትርኢት የቀረበ ሲሆን በሁለቱም ተቋማት ተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች እንዲሁም የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች በርካታ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ ያሉ የምርምርና ፈጠራ ሥራ መሰረተ ልማቶች ተጎብኝተዋል::

በፕሮግራሙ ላይ ከ150 በላይ የሚሆኑ ከሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የኢንዱስትሪ ዘርፋ የስራ ኃላፊዎች: ከሀዋሳና ይርጋዓለም ኢንዱስትሪ ፖርኮች እንዲሁም ሌሎች ከግልና የመንግስት ኢንዱስትሪዎች የተወጣጡ ኃላፊዎችና የኢንዱስትሪ ባለቤቶች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ወደፊት በምን መልኩ አብረው መስራት እንደሚገባና ባሉ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል::

ዶ/ር ታፈሰ በውይይቱ ማጠቃለያ ንግግራቸው "ከዚህ በኃላ በከፍተኛ ጥራት የተማረና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ኢንዱስትሪው የሚፈልገው አይነት የሰው ኃይል በማፍራት: ችግር የሚተነትን ሳይሆን ችግር ፈቺ ምርምር በመስራት እንዲሁም ቴክኖሎጂና ፈጠራን በሚያበረታቱ አሰራሮች የኢንዱስትሪውን ዘርፍ በመደገፍ ላይ ትኩረት ይደረጋል:: ለዚህም ዩኒቨርሲቲ እንደ እውቀት ምንጭ: ኢንዱስትሪው እንደ ካፒታል ባለቤት እና የፖለቲካ አመራሩ ደግሞ ለሕዝብ የገባው ኃላፊነት እንዳለበት ባለድርሻ አካል የሶስቱ ቅንጅትና ተናብቦ መስራት አሁን ግዜው የሚጠይቀው አካሄድ ነው" ብለዋል::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: [email protected]
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa




ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የቅድመ ዝግጀት እና መከላከል ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል
ይንንም ተግባር ከሳይንስ እና ከፍተኛ ት/ት ሚኒስተር አቅጣጫ ከተሠጠበት ዕለት ጀምሮ በዩኒቨርሰቲው ፕሬዝዳንት የሚመራ እና የዩኒቨርሰቲውን ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና ሌሎች አመራሮችን የያዘ ዓብይ ኮሚቴ በማዋቀር ሥራ ጀምሯል፡፡
ዓብይ ኮሚቴው ሁለት ንዑሳን ኮሚቴዎችን ያዋቀረ ሲሆን፤የመጀሪያው በዩኒቨርሲቲው አስ/ተማ/አገ/ ም/ፕሬዝዳንት የሚመራ እና የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር፤የተማሪዎች መማክርት አባላትን እንዲሁም የተማሪ ክበባት ተወካዩችን የያዘ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በዲኖች የሚመራ የየካምፓስ ቴክኒካል ኮሚቴ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከሚገኙ ባለሙያዎች የተውጣጣ የህክምና ቡድን ተዋቅሯል::
ዓብይ ኮሚቴው በየካምፓሱ ያለውን ሁኔታ በአካል ዞሮ በማየት የቅድመ ዝግጅት ሥራውን ካስጀመረ በኃላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች እና መልዕክቶችን አስተላልፏል
• ተማሪዎች ከተከሰተው የኮሮና ሥጋት ጋር ተያይዞ በዚህ ወቅት ወደ ቤተሰብ መሄድ፤በጉዞ ወቅት ይበልጥ ተጋለጭነትን ስለሚጨምር በየጊቢያቸው ሆነው ከዩኒቨረሲቲው ሕክምና ቡድን እና ከበጎፍቃደኛ ተማሪዎች የሚሠጣቸውን መመሪያ መፈጸም አለባቸው፡፡
• የምግብ ሠዓትን በተመለከተ፤ የተማሪዎችን መጠጋጋት እና መጨናነቅ ለማስወገድ ሲባል ከዚህ በታች ያለው የሠዓት ማሻሻያ ተደርጓል፡
ቁርስ- 1፡00 እስከ 3፡00
ምሳ- 5፡30 እስከ 8፡00
እራት-11፡00 እስከ 2፡00
• የ non-café ተማሪዎችን በተመለከተ ይህ ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ የተለየ አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ካልቻሉ ጊዚያዊ የመመገቢያ መታወቅያ ተሰጥቷቸው በዩኒቨርሲቲው ካፌ መመገብ ይችላሉ፡፡
• ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸው የሚሰጧቸውን አሳይመንት እና ንባብ በአግባቡ መሥራት አለባቸው፡፡
• የቤተ-መፅህፍት አገልግሎት እስክ ሌሊቱ 6፡00 የተራዘመ ስለሆነ፤ተማሪዎች መጨናነቅን ባስወገደ መልኩ በተለያየ ሰዓት እየገቡ መጠቀም ይችላሉ፡፡
• ከጊቢ ውጭ መውጣት እና መግባትን በተመለከተ፤ከላይ እንደተጠቀሰው ወደ ቤተሰብ ወይም አቅራቢያ ላይ ወዳሉ ከተሞች መሄድ ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን፤ ይህንንም ለማስፈጸመም ተማሪዎች በአስገዳጅ ምክንያት ከጊቢ መውጣት ከፈለጉ መታወቂያቸውን በማስያዝ የሚወጡበት ሠዓት ተመዝግቦ ለአጭር ሰዓት ብቻ ከጊቢ ወጥተው መመለስ ይችላሉ፡፡
• ተማሪዎች በጊቢ ውስጥ የሚሠጡ የባንክ እና ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በመጠቀም አላስፈላጊ የሆኑ የጊቢ ውጪ እንቅስቃሴዎችን ማቆም ይኖርባቸዋል፡፡
• ተማሪዎች መውሰድ ስላለባቸው ጥንቃቄ ከጤና ባለሙያዎች እና ከታማኝ ምንጮች ብቻ መረጃዎችን በመቀበል፤ ከዪኒቨርሲቲው እና በግላቸው በሚያገኟቸው የንፅህና መጠበቂያዎች የግል ንፅህናቸውን በመጠበቅ እና በመረጋጋት ይህንን ጊዜ በጋራ ለማለፍ ጥርት ማድረግ አለባቸው፡፡
በመጨረሻም፤ትኩሳት፤ለመተንፈስ መቸገር፤ የትንፋሽ መቆራረጥ እና ሳል ካገጠመ ወይንም ይህንን ምልክት የሚያሳይ ተማሪ ካለ በነፃ ስልክ መሥመር 6929 ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ ጤና ቢሮ ጥቆማ መስጠት ይቻላል፡፡

 በመተባበር፤በመደማመጥ እና የሚሰጡ መመሪያዎችን በስነምግባር በመፈፀም ይህንን ወቅት ማለፍ እንችላለን!!!


The 2nd Ethiopian Universities Research and Community Service Vice Presidents' Forum organized by MoSHE and Hawassa University

February 28-29/2020

Hawassa


Representatives of Partner Universities and Organizations Visited HU
Hawassa University received a group of researchers from the USA and partner organizations in relation to an ongoing project entitled "EQUIP-Strengthening Smallholder Livestock Systems for the Future" on 20 Feb. 2020. The purpose of the visit was to observe the progress of the project that is being implemented for five years (2017-2022) with the goal of improving the incomes, livelihoods and nutrition of smallholders in Ethiopia and Burkina Faso.
Prof. Adugna Tolera and lead researchers from University of Florida and University of California-Davis provided explanation about the overarching purpose of the project, the various activities being carried out and the anticipated goals to the President of HU, Dr. Ayano Berasso, the Vice President for Academic Affairs (VPAA), Dr. Fisiha Getachew, and other participants.
Finally, both the President and the VPAA of appreciated the joint effort exerted by all researchers involved in the project and expressed HU's support toward its success.


#የሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ_የቦርድ_ስብሰባ
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትርና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሌሎች የቦርድ አባላት ጋር በመሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስብሰባ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በስብሰባውም÷ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉና ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ በመጨረሻም ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል፡፡


Hawassa University hosted six month performance report evaluation!
Date Published: 08 Feb. 2020
Hawassa University has conducted a staff meeting aimed at evaluating half year reports of colleges and IoT for two consecutive days from 07-08 February 2020.
The first day of the meeting revolves around six months report of four colleges (WG-CFNR, CLG, CAG, CSHH), two campuses (Awada and Daye) and the Institute of Techonlogy (IoT). This was accompanied by comments and questions on the reports presented by the respective Dean's and the Scientific Director of IoT from HU staff. The staff had also raised their concern and opinion on current issues within HU.
The second day of the discussion resumed with questions and comments from the staff. Then the president, Dr. Ayano Berasso, and the Vice President for Academic Affairs, Dr. Fisiha Getachew, addressed most of the issues during the morning session. Likewise, Dr. Mesay, Vice President for Administration and Student Affairs and Ato Denbeshu Neare, Vice President for Business and Development, and presenters had reflected on major issues focusing on them.

The discussion was concluded at 1:30PM.


Happening Now!
Second day of staff discussion on annual report of colleges is being held at Hawassa University.
More will come soon!


#የሀዘን_መግለጫ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በወንዶ ገነት ካምፓስ የጄኔራል ፎረስትሪ ት/ክፍል 3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው በርዬ አወቀ አበበ በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ በማለፉ ዩኒቨርሲቲው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቡ፣ ለዘመዶቹ እና ለጓደኞቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡


Hawassa University received Mrs. Corrie Young Associate Executive Director-Project and Network, Academics without Borders (AWB).
A fruitful discussion was done about potential collaboration platforms with AWB on training, education, research and community services.
HU agreed to receive voluntaries from AWB in different fields of studies. AWB also promised do its best in fulfilling the request of HU and will continue working to support HU for quality of education, research and community service.


Hawassa University hosted Inception workshop on Green People’s Energy(GPE);Domestic Biogas Project
By: Sileshi Negash
Hawassa University Office of Vice president for research and technology transfer hosted Inception workshop on GPE, Domestic Biogas Project to improve rural livelihood in Ethiopia at Hawassa University College of Agriculture.
Dr. Eng. Fisha Getachew, Vice President for Academic Affairs HU, said that in developing countries people rely on traditional cook stoves and open fires to burn biomass or coal for heating and cooking. This practice causes harmful local air pollution and increases danger from fire hazards, serious local environmental damage including desertification which can be caused by excessive harvesting of wood and other combustible materials.
Mrs. Hiwot Abayneh, Project Coordinator said that this project aims at improving the rural livelihood through construction of biogas plant in Damot Woyde and Duguna Fango districts of SNNPRS. The small scale domestic biogas plant will be used for light and cooking.
Moreover, the bi-product can be used as organic fertilizer and the benefits of the technology in general includes improving health, reducing workload for women and children, improving education, preventing deforestation, improving soil fertility, job creation for local community and promoting rural youth entrepreneurship.
The project will be implemented by Hawassa University in collaboration with Water, Mines and Energy Bureau at different levels in the Region and GIZ/EnDev.
On the Workshop representatives of partners; Mr. Tektel Matewos, Alternative Energy Development and Technology Transfer Director, Regional Water, Mine and Energy Bureau, Mr. Magnus Schmid, Program Director, Green Innovation Center (GIC, GiZ) and Mr. David Otieno, Program Director, Energizing Development (EnDev , GiZ) were present.


Hawassa University hosted Inception workshop on Domestic Biogas Project


የሀዘን መግለጫ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነው ሱራፌል ሰሎሞን ፀጋዬ በትናንትው ዕለት አመሻሽ ላይ በደረሰበት ጉዳት ወደ ሪፌራል ሆስፒታል ተወስዶ ሕይወቱን ለማዳን ከፍተኛ ርብርብ ቢደረግም ሳይሳካ በመቅረቱ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡
ዩኒቨርሲቲውም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለተማሪ ሱራፌል ቤተሰብና ዘመድ ወዳጆቹም መጽናናትን እየተመኘ ከተማሪው ሞት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተካሄደባቸው በመሆኑ ምርመራው እንደተጠናቀቀ ጥፋተኛ ሆነው በሚገኙት ላይ በወንጀል ህግና በአካዳሚክ ዲሲፕሊን ደንብ መሠረት አስፈላጊው እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ይገልጻል፡፡


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Hawassa University Reasonable Visionaries Club (RVC) in Collaboration with Office of External Relations & Communications


የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያንቺ ንቅናቄ ( Yanchi movement ) ለሶስት ቀን በሚቆየው የሴት ልጅ ጥቃትን በመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ ዝግጅቱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ16 ቀን ንቅናቄ አንድ አካል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸውልናል፡፡ በዚህ ንቅናቄ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ሌሎች ክበባትም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በሌላ በኩል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው "መራሂት ክበብ" አትኩሮቱን ሴት ተማሪዎችን በማብቃት ላይ አድርጎ እየሰራ ሲሆን ለሴት ተማሪዎች የፅዳት መጠበቂያ የሚሆን 88 ካርቶን ሞዴስ በመግዛት ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሴቶች ህፃናት ወጣቶች እና ኤችአይቪ ኤድስ ዳይሬክትቶሬት አስረክበዋል። የመጀመሪያውን ድጋፋቸውንም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ በሆነው በአዋዳ ካምፓስ አድርገዋል።
ተማሪዎቻችን እየሰራችሁት ላለው መልካም ስራና ለሌሎች ወጣቶች ትምህርት የሚሰጥ ተግባር ላይ በመሳተፋችሁ ያለንን ምስጋና እናቀርባለን!
#HawassaUniversity

16 last posts shown.

2 171

subscribers
Channel statistics
OSZAR »